The main office of the Ethiopian Family Department Association wants to sell a variety of used vehicles in an open auction.

የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማህበር

ያገለገሉ ተሸከርካሪዎችን ጨረታ ለመሸጥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ


Similar Jobs in Ethiopia
Learn more about The main office of the Ethiopian Family Department Association
The main office of the Ethiopian Family Department Association jobs in Ethiopia

የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማህበር ዋናው መ/ቤት የተለያዩ ያገለገሉ ተሸከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልግ ህጋዊ ድርጅትም ሆነ ግለሰብ በጨረታው ላይ መወዳደር ይችላል፡፡

የጨረታውን ዶክመንት ስለመግዛት፡ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 ብቻ በመክፈል ከሰኞ ህዳር 12 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማህበር ዋናው መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 ቀርበው የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶችና ሁኔታዎች መሟላትና ማወቅ ይጠበቅባቸዋል፡

  1. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣ በኃላ ከዚህ በታች በተገለፀው ፕሮግራም መሰረት በስራ ሰአት የሚሸጡትን ያገለገሉ ተሸከርካሪዎች በአዲስ አበባ ከተማ መሷለኪያ/ሪቼ አካባቢ በሚገኘው የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማህበር ዋናው መስሪያ ቤት ቤት በመገኘት ከሰኞ ህዳር 26 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ አርብ ህዳር 30 ቀን 2015 ዓ.ም ባሉት አምስት ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በማኅበሩ ዋና መ/ቤት ተገኝተው የሚሸጡ ተሸከርካሪዎችን መመልከት ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች ሊገዙት ለሚፈልጉት ተሸከርካሪ የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታው ዶክመንት ውስጥ በተዘጋጀው የመጫረቻ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ አስገብተው ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያው በሪፖርተር ጋዜጣ የአማርኛ እትም ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ከወጣበት ከእሁድ ህዳር 11 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኞ ታህሳስ 3 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ በድርጅቱ  አድራሻ ማለትም በአዲስ አበባ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ፣ ሪቼ/መሷለኪያ አካባቢ በሚገኘው የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማህበር ዋናው መ/ቤት ግቢ ውስጥ በሚገኘው$ ቢሮ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ለእያንዳንዱ ተሸከርካሪ የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 20 በመቶ በኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማህበር ስም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ/ሲፒኦ/ ከጨረታ ዋጋ ማቅረቢያው ጋር በታሸገ ፖስታ ውስጥ አብሮ ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ጨረታው ሰኞ ታህሳስ 3 ቀን 2015 ዓ.ም በ6፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ በጨረታው ለመገኘት በፈቀዱና በቻሉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማህበር ዋናው መ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚከፈት ሲሆን አሸናፊው እንደታወቀ ወዲያው ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ሲፒኦ ታሳቢ በማድረግ ቀሪውን ገንዘብ በ5 ቀናት ውስጥ ከፍለው ንብረቱን የማንሳት ግዴታ አለባቸው፡፡ በጨረታው አሸንፈው ከፍለው ለማይወስዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ ያስያዙት ገንዘብ ገቢ ይሆናል፡፡ የጨረታ አሸናፊዎች የገዙአቸውን ተሽከርካሪዎች የማጓጓዣ ወጪዎችንና ሌሎች ተያያዥ ወጪዎችን በሙሉ ይሸፍናሉ፡፡
  5. በጨረታው ለሚሸነፉት ያስያዙት የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ/ቢድ ቦንድ/ የጨረታ አሸናፊው ሙሉ ክፍያውን እንደፈጸመ የሚመለስላቸው ይሆናል፡፡
  6. ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ በማንኛውም ወቅት የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ በኢትዮጰያ ቤተሰብ መምሪያ ማህበር

  ዋናው /ቤት

 ስልክ251 -11 467 2300 ወይም 251 -11 467 2216

.ቁጥር 5716

አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

Job Info
Job Category: Tenders in Ethiopia
Job Type: Full-time
Deadline of this Job: 12 December 2022
Duty Station: Addis Ababa
Posted: 22-11-2022
No of Jobs: 1
Start Publishing: 22-11-2022
Stop Publishing (Put date of 2030): 22-11-2065
Apply Now

Notification Board:

Join a Focused Community on job search to uncover both advertised and non-advertised jobs that you may not be aware of. A jobs WhatsApp Group Community can ensure that you know the opportunities happening around you and a jobs Facebook Group Community provides an opportunity to discuss with employers who need to fill urgent position. Click the links to join. You can view previously sent Email Alerts here incase you missed them and Subscribe so that you never miss out.

Caution: Never Pay Money in a Recruitment Process.

Some smart scams can trick you into paying for Psychometric Tests.