Anbesa International Bank SC 18th regular and 6th emergency general meetings of shareholders

Ø    በንግድ  ምዝገባና  ፈቃድ  አሰጣጥ  አዋጅ  ቁጥር 67/1989 አንቀፅ 23 መሰረትየንግድ ምዝገባ ቁጥር 05/2/13118/99 የተመዘገበ

Ø    ዋና መስሪያ ቤት – ኃይሌ ገ/ስላሴ ጎዳና – ሌክስ ፕላዛ ህንጻ – አዲስ አበባ

Ø     የባንኩ የተከፈለ ካፒታል ብር 2,588,669,333 (እ.አ.አ ኦክቶበር/2022 መጨረሻ)

Similar Jobs in Ethiopia
Learn more about Anbesa International Bank SC
Anbesa International Bank SC jobs in Ethiopia

የባለአ ክስዮኖች 18ኛ መደበኛ እና የ6ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔዎች  የስብሰባ ጥሪ

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. 18ኛ መደበኛ እና 6ኛ አስቸኳይ የባለአክስዮኖች ጠቅላላ ጉባዔዎች ቅዳሜ ታህሳስ 08 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ በሒልተን ሆቴል የስብሰባ አዳራሽ የሚያካሂድ በመሆኑ የባንኩ ባለአክሲዮኖች በተጠቀሰው ቀን፣ ቦታና ሰዓት ተገኝተው በጉባዔዎቹ እንዲሳተፉ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን በአክብሮት ያቀርባል፡፡

የ18 ኛ  መደበኛ ጠቅላላ አጀን ዳዎች ፡

  1. 1. የጉባዔው አጀንዳ ማጽደቅ፣
  2. 2. የአዳዲስ አክሲዮኖች ዝውውር ማጽደቅ፣
  3. 3. እ.ኤ.አ የ2021/2022 የሒሳብ ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርት ማድመጥና ተወያይቶ ማጽደቅ፣
  4. 4. እ.ኤ.አ የ2021/2022 የሒሳብ ዓመት የውጪ ኦዲተሮች ሪፖርት፣ የሀብትና ዕዳ ሚዛን እንዲሁም የትርፍና ኪሣራ መግለጫ ማድመጥና ተወያይቶ ማጽደቅ፣
  1. 5. እ.ኤ.አ በ2021/2022 የሒሳብ ዓመት የተጣራ ትርፍ አደላደልና አከፋፈል ላይ ውሳኔ መስጠት፣
  2. 6. እ.ኤ.አ የ2022/2023 የሒሳብ ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ወርሃዊ አበልና ዓመታዊ የአገልግሎት ክፍያ መወሰን፣
  3. 7. የዳይሬክተሮች ቦርድ ምልመላና አስመራጭ ኮሚቴ ሪፖርት ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፣
  4. 8. የዳይሬክተሮች ቦርድ ምርጫ ማካሄድ፣
  5. 9. የስብሰባው ቃለ ጉባዔ ማጽደቅ፡፡


የ6 
ኛ   አስቸኳይ ጠቅላላ  ጉባኤ  አጀንዳዎች

  1. 1. በቀረበው አጀንዳ ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፣
  2. 2. በተሻሻለው የባንኩ የመመስረቻ ፅሑፍ ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፣
  3. 3. የባንኩን የአንድ አክስዮን ዋጋ ማሻሻል፣
  4. 4. የባንኩን ካፒታል ለማሳደግ በዳይሬክተሮች ቦርድ በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ተወያይቶ መወሰን፣
  5. 5. የስብሰባው ቃለ ጉባዔ ማጽደቅ፡፡

 ማሳ ሰቢያ  ፡-

  • በጉባዔዎቹ ላይ በግንባር መገኘት የማትችሉ ባለአክሲዮኖች ከስብሰባው ዕለት ቢያንስ ከሶስት ቀናት በፊት ኃይሌ ገ/ስላሴ ጎዳና – ሌክስ ፕላዛ ህንጻ በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት የህግ መምሪያ 7ኛ ፎቅ በመቅረብ ባንኩ ለዚሁ ጉዳይ ባዘጋጀው የውክልና ቅፅ ላይ በመሙላት ተወካዮቻችሁን ማሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  • የባለአክስዮኖች ህጋዊ ተወካዮች የውክልና ስልጣን የተሠጠበት ሕጋዊ ሰነድ ይዛችሁ በመቅረብ በጉባዔዎቹ ላይ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡
  • በጉባዔዎቹ በአካል የምትገኙም ሆነ በባንኩ ቀርባችሁ ውክልና የምትሰጡ ባለአክስዮኖች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላችሁ መሆኑን ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ መሆናችሁን የሚያሳይ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፖስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ ዋናውንና አንድ ኮፒ ይዛችሁ እንድትቀርቡ፡፡
  • ውል ለማዋዋል ሥልጣን በተሰጠው አካል የተረጋገጠና በጉባኤዎቹ ለመካፈል የሚያስችል ውክልና

ይዛችሁ ለምትቀርቡ ተወካዮች የወካያችሁን ማንነት የሚያረጋግጥ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፖስፖርት ኮፒ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡

  • ምልዓተ ጉባዔዎቹ ተወያይቶ የሚያስተላልፏቸው ውሳኔዎች በጉባዔዎቹ ባልተገኙ አባላት ላይም የፀና ይሆናል፡፡
  • ባንኩ የባለአክስዮኖችን የመለያ ቁጥር ባስመዘገባችሁት የተንቀሳቃሽ ስልክ የሚላክ ሲሆን፤ የመለያ ቁጥራችሁን በስብሰባው ዕለት ይዛችሁ እንድትቀርቡ በአፅምኦት እንጠይቃለን፡፡
  • የተሻሻለው የመመስረቻ ፅሑፍ ረቂቅ ሰነድ ከባንኩ ዋና መ/ቤት የህግ አገልግሎት መምሪያ ቀርባችሁ መውሰድ ትችላላችሁ ወይም በባንኩ ድረ-ገፅ https://anbesabank.com/   ላይ የተቀመጠ በመሆኑ ሰነዱን በማውረድ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  • በጉባዔዎቹ የምትገኙ ተሳታፊዎች የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ

እንደሚኖርባችሁ ለማስታወስ እንወዳለን፡፡

የዳይሬክተሮች ቦርድ አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ

የስኬትዎ አጋር!

Job Info
Job Category: Tenders in Ethiopia
Job Type: Full-time
Deadline of this Job: 17 December 2022
Duty Station: Addis Ababa
Posted: 22-11-2022
No of Jobs: 1
Start Publishing: 22-11-2022
Stop Publishing (Put date of 2030): 22-11-2065
Apply Now

Notification Board:

Join a Focused Community on job search to uncover both advertised and non-advertised jobs that you may not be aware of. A jobs WhatsApp Group Community can ensure that you know the opportunities happening around you and a jobs Facebook Group Community provides an opportunity to discuss with employers who need to fill urgent position. Click the links to join. You can view previously sent Email Alerts here incase you missed them and Subscribe so that you never miss out.

Caution: Never Pay Money in a Recruitment Process.

Some smart scams can trick you into paying for Psychometric Tests.